የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ መስፈርቱን የሚያሟሉ የድህረምረቃ ትምህርት ፈላጊዎችን በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመደበኛ እና በተከታታይ የድህረ-ምረቃ መርሀግብሮች በማስተርስ ዲግሪ በ2010 ዓ.ም አንደኛ መንፈቀ አመት ትምህርት ለመጀመር ማስታወቂያ ማዉጣቱ ይታወሳል፡፡ ማስታወቂያዉን ተከትሎ  ለፈተና መቅረብ የሚያስችል የአመልካች ቁጥር የቀረበባቸዉ ትምህርት መስኮች፤ 

  1. Master of Business Administration
  2. Accounting & Finance
  3. Urban Socioeconomic Development Planning
  4. Athletics Coaching
  5. Educational Planning and Management
  6. Ecosystem and Biodiversity Conservation
  7. Teaching Amharic ሲሆኑ፤

ፈተና የሚሰጠዉ ሰኞ ጥቅምት 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ስለሆነ ባመለከታችሁበት ትምህርት ክፍል በመገኘት ፈተናዉን እንድትወስዱ እናሳዉቃለን፡፡ፈተናዉን ወስደዉ፤ እንዲሁም ሌሎች የመመልመያ መስፈርቶችን  አሟልተዉ ከአመልካቾች መካከል በቂ የተመዝጋቢ ቁጥር በተገኘበት ብቻ ትምህርቱ እንደሚጀምር በድጋሜ እንገልጻለን፡፡

 ግልባጭ፤

  • ለፕሬዝዳንት ጽ/ቤት
  • ለአካዳሚክ ጉ/ም/ፕሬዝዳንትጽ/ቤት
  • ለድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ዳይሬክቶሬት

ለሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት