የኮተቤ  ሜትሮፖሊታን  ዩኒቨርሲቲ  በ2010 ዓ/ም  የትምህርት ዘመን  በተከታታይና ርቀት ትምህርት መርሃ ግብር በተለያዩ  የስልጠና መስኮች  ማለትም ፤ በመጀመሪያ ዲግሪ  በማታ (ከሰኞ እስከ  እሁድ) ወይም በሳምንት መጨረሻ (ቅዳሜና እሁድ ብቻ)፣ በዲፕሎማና  በሰርቲፊኬት  ማታ (ከሰኞ እስከ እሁድ) አዲስ አመልካቾችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡በመሆኑም  መስፈርቱን የምታሟሉ ትምህርት ፈላጊዎች ከመስከረም 19 እስከ መስከረም 26/2010 ዓ/ም  ድረስ  ዘወትር  በስራ ሰዓት (ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ) ኮተቤ ሜትሮፖሊታን  ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና  አሉሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ማመልክት የምትችሉ መሆኑንና ዝርዝር የመግቢያ መስፈርት፣ የስልጠና መስኮችንና  መረጃዎችን በውስጥ ማስታወቂያ  ላይ  ማግኘት የሚቻል መሆኑን  ያስታውቃል፡፡ 

  ማሳሰቢያ፡-

ለማመልከት፤

1. የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ፣

2. ለዲግሪ ብር 50.00፣ ለዲፕሎማና ሰርቲፊኬት ብር 30.00 መክፈል የሚያስፈልግ ሲሆን፣

3. በማንኛውም የስልጠና መስክ አዲስ አመልካቾችን ተቀብሎ ማሰልጠን የሚጀመረው  በመስኩ በቂ አመልካቾች ሲኖሩ ብቻ መሆኑንም ያስታውቃል፡፡ 

 

የኮተቤ  ሜትሮፖሊታን  ዩኒቨርሲቲ  በ2010 ዓ/ም  የትምህርት ዘመን  በተለያዩ  የስልጠና መስኮች  ማለትም ፤

 

 1. በመጀመሪያ ዲግሪ በማታ ( ከሰኞ  እስከ  እሁድ) ወይም  በሳምንት መጨረሻ (ቅዳሜና እሁድ ብቻ)
 2. በዲፕሎማና  በሰርቲፊኬት   ማታ ( ከሰኞ እስከ  እሁድ ብቻ)

አዲስ አመልካቾችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡

 

በመሆኑም  መስፈርቱን የምታሟሉ  ከመስከረም  19  እስከ መስከረም 26  2010 ዓ/ም  ድረስ  ዘወትር  በስራ ሰዓት (ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ) ኮተቤ ሜትሮፖሊታን  ዩኒቨርሲቲ  ሬጅስትራርና  አሉሙናይ  ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ማመልክት የምትችሉ መሆኑንና ዝርዝር የስልጠና መስኮችንና  መረጃዎችን በውስጥ ማስታወቂያ  ወይም በዩኒቨርሲቲው ድረገጽ  www.kmu.edu.et  ላይ  ማግኘት የሚቻል መሆኑን  ያስታውቃል፡፡

 

የመገቢያ መስፈርት

 1. ለመጀመሪያ ዲግሪ በትምህርት ሚኒስቴር የመግቢያ መስፈርት ፤

         የመሰናዶ ፈተና ለወሰዱ፡-

 • በ2009 ዓ/ም 295 እና ከዚያ በላይ                      
 • በ2008 ዓ/ም 295 እና ከዚያ በላይ
 • በ2007 ዓ/ም 275 እና ከዚያ በላይ
 • በ2006 ዓ/ም 250 እና ከዚያ በላይ
 • በ2005 ዓ/ም 265 እና ከዚያ በላይ
 • በ2004 ዓ/ም 265 እና ከዚያ በላይ
 • በ2003 ዓ/ም 265 እና ከዚያ በላይ
 • በ2002 ዓ/ም 280 እና ከዚያ በላይ
 • በ2001 ዓ/ም 200 እና ከዚያ በላይ
 • ከ1995-2000 ዓ/ም የመሰናዶ ፈተና ወስደው ውጤት ያስመዘገቡ

 

          ከ1994 ዓ/ም በፊት ዲፕሎማ ያጠናቀቁ ፡-

         ከ1994 በፊት ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በዲፕሎማ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ እና  ከ1994 በኋላ ከየትኛውም ተቋም ትምህርታቸውን በ10+3 ወይም በደረጃ 4 ያጠናቀቁ ሆነው የደረጃ 4 የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የሚያቀርቡ

          እውቅና ካለው ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ዲፕሎማ የተመረቁና የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና የሚያልፉ

          ዲግሪ ያላቸው በሌላ ዲግሪ ለመማር በማንኛውም መስክ ማመልከት ይችላሉ ፡፡

2. ለዲፕሎማ፤

 • በ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና (EGSEC) ወይም በቀድሞው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና (ESLCE) 2.00 እና ከዚያ በላይ ያላቸው ወይም
 • እውቅና ካለው የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ወይም ተቋም በመምህርነት ሰርቲፊኬት ተመርቀው 50%  (2.00) ያላቸው ወይም
 • እውቅና ካለው ኮሌጅ ወይም ተቋም በቅድመ መደበኛ መምህርነት የአንድ ዓመት ስልጠና  ሰርቲፊኬት ያላቸው

3. ለቅድመ መደበኛ ሰርቲፊኬት፤

 • በ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ቢያንስ 2.00 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ

 

ማሳሰቢያ፡-

1. በሀገር አቀፍ ደረጃ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ላልተዘጋጀላቸው የትምህርት ዘርፎች ዩኒቨርሲቲው የመግቢያ ፈተና ያዘጋጃል !!
2. ለማመልከት የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ፣
3. ለዲግሪ ብር 50.00፣ ለዲፕሎማና ሰርቲፊኬት ብር 30.00 መክፈል የሚያስፈልግ ሲሆን፣
4. በማንኛውም የስልጠና መስክ አዲስ አመልካቾችን ተቀብሎ ማሰልጠን የሚጀመረው በመስኩ በቂ አመልካቾች ሲኖሩ ብቻ መሆኑንም
ያስታውቃል፡፡

 

የስልጠና መስኮች

 1. አማርኛ (Amharic)
 2. እንግሊዝኛ (English)
 3. ታሪክ (History)
 4. ጂኦግራፊ (Geography & Environmental Studies)
 5. ስነዜጋና ስነምግባር (Civics  and Ethical Education)
 6. ባዮሎጂ (Biology)
 7. ኬሚስትሪ (Chemistry)
 8. ፊዚክስ (Physics)
 9. ሂሳብ (Mathematics)
 10. ስፖርት ሳይንስ (Sport Science)
 11. ኮምፒውተር ሳይንስ (Computer Science)
 12. አካባቢ ሳይንስ (Environmental Science)
 13. የከተማ መሬት አስተዳደር (Urban land Management)
 14. የከተማ ትራንስፖርት አስተዳደር (Urban Transport Management)
 15. የከተማ  ኤንቫይሮን ሜንታል አስተዳደር (Urban Environmental Management)
 16. ስራፈጠራና ንግድ አስተዳደር (Entrepreneurship &Business management)
 17. አካውንቲንግና ፋይናንስ (Accounting and Finance)
 18. ማኔጅመንት (Management)
 19. ኤኮኖሚክስ (Economics)
20. ስኩል ሳይኮሎጂ (School  Psychology)

 

 መሆናቸውን ያስታውቃል፡፡

  የኮተቤ  ሜትሮፖሊታን  ዩኒቨርሲቲ  የተከታታይና  ርቀት ትምህርት  ዳይሬክቶሬት